You are here: HomeNews/Events

News and Events

ቀደምት ሆነው በአዲስ አበባ ውስጥ ከተመሠረቱት ስድስት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያዎች መካከል አንደኛ የሆነችውና በመሃከለኛው የአዲስ አበባ ክፍል ላይ የምትገኘው የቀበና አጥቢያ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን በአምልኮ ቦታ ላይ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ችግሮች የገጠሟት ሲሆን ይህም ችግር መደበኛ የእሁድ አምልኮ ፕሮግራሟን እስከ ማቋረጥ የደረሰበትም ወቅት እንደነበር ፓስተር ዶክተር የምሩ ጥላሁን ገልጸውልናል፡፡ አጥቢያይቱ በቀበሌ አዳራሽ፣ በኖርዌጂያን ሚሽን አዳራሽና በቀድሞው የግብርና ሚ/ር አዳራሽ እየተዘዋወረች የአምልኮ ፕሮግራሞቿን ስታካሂድ ቆይታ በኋላ ግን በደርግ ዘመን…
በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የሚካሄደው ወርኀዊው የመጽሐፍ ግምገማ መርኀ ግብር ባለፈው እሑድ ግንቦት 2 ቀን፣ 2007 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡ በዕለቱ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ በጳውሎስ ... Posted by Hintset Christian Society- ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር on Wednesday, May 13, 2015
ሪዲምሚዲያ በትንሳኤ ዋዜማ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የግጥም ምሽት በገነት ሆቴል አዘጋጅቷል፡፡ የፕሮግራሙ ዓላማ በአዳማ ለሚደረገው ቀጣይ የወንጌል ዐውደ-ርዕይ ገቢ ለማሰባሰብ ነው፡፡ የግጥም ምሽቱ ልዩ ገጣሚያንን፣ አኩስቲክ ሙዚቃና መዝሙሮች የሚቀርቡበት ምሽት ነው፡፡ ፕሮግራሙ ሚያዝያ 3 2007 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን የዝግጅቱ ቦታ ከሜክሲቆ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው በገነት ሆቴል ፣ መግቢያውም 200 ብር ነው፡፡ ጓደኞቻችሁን ጋብዙ፤ እናንተም አያምልጣችሁ! ሪዲምሚዲያ ፈጠራ በተሞላበት…
The Ethiopian Graduate School of Theology (EGST) was established in 1997 in response to a growing need perceived within the Churches of Ethiopia to provide a contextually relevant graduate level theological education within the country. EGST is Christian institution that exists to equip Christ-like women and men through theological and related studies and to stimulate research for the service of Church and Society in Ethiopia and beyond. Currently, EGST offers…
ድንቅ ስጦታ በሚል ርእስ ልዩ የገና መዝሙር ኮንሰርት ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በምስራቅ አዲስ አበባ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። የዚህ የገና መዝሙር ኮንሰርት ዓላማ የሰዎች ሁሉ ዓይኖች ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ላይ እንዲሆን፥ ትልቁ ስጦታ እሱ እራሱ እንደሆነ እንዲታወቅና በዕለቱም ሰው እግዚአብሔርን ከመዝሙር አምልኮ ባሻገር በተግባር ወላጅ ያጡና ችግረኛ ሕጻናትን ባለው ነገር ማለትም ጊዜውን፥ እውቀቱን ፥ ገንዘቡን ፥ በሚችለው ሁሉ በመስጠት እንዲያመልክ ነው። ዳዊት…
በሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን የተጻፈውና “የደነበረው በቅሎ”፡ የአስተምህሮ “ልጓም” ይሻል የሚል ርእስ ያለው ዐዲስ መጽሐፍ በሕዳር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተመረቀ። የመጽሐፉ ምረቃ በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች (IEC/ETC) የተካሄደ ሲኾን እጅግ በርካታ ታዳሚዎች ተገኝተውበታል። በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የታወቁ አገልጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የጸሐፊው ወዳጆችና አናባቢዎች የታደሙበት ይህ የምረቃ ሥነ ሥርዐት ከቀኑ 9፡00-12፡00 የዘለቀ ነበር። መርሐ ግብሩ በአቶ ዘላለም አበበ እና በወይዘሪት ትዕግሥት ተስፋዬ የመድረክ አስተባባሪነት የተመራ ሲኾን፣…

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 143 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.