You are here: HomeNews/Events

News and Events

የግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ በወንጌል ስርጭት ፣ ደቀ መዛሙርትን በማፍራት፣ በቤተ ክርስቲያን ተከላና በመሪዎች እድገት ዙሪያ ከአብተ ክርስቲያናት እና መንፈሳዊ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል። በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ከዛብሎን አገልግሎት ጋር እና ከወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር አዲስ ዌቭ በሚል ስያሜ ከነሐሴ 2007ዓ/ም ጀምሮ ለአስራ ስምንት ወራት የሚዘልቅ ታላቅ የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጀት ላይ እንገኛለን። የዚህ ፕሮግራም አካል እና የመጅመሪያ ምዕራፍ የሆነውን ‘አድሰን’፣’ሙላን’፣’ላከን’ በሚል ትኩረት የተዘጋጀውን ልዩ የጸሎትና የወንጌል…
የፊታችን ነሐሴ 17 እሁድ ከ 8 ሰዓት ጀምሮ Turning Point በሚል ርዕስ በባይብል አርሚ - ኪንግደም አጥቢያ (ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው) በአይነቱ ልዩ የሆነ የወጣቶች ፕሮግራም ተዘጋጅቶአል ፡፡ ለፕሮግራሙ የተሰጠው ስያሜ እና እየተደረገ ያለው ዝግጅት ከተለመደው ወጣ እንደሚል የፕሮግራሙ አዘጋጆች የገለጹልን ሲሆን ይህ ፕሮግራም በየመፅሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም ዐቀፍ ቤተክርስቲያን - የወጣቶች አገልግሎት እና ጋፕስ ዓለም ዐቀፍ ሚኒስትሪ በመተባበር የተዘጋጀ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ፕሮግራሙ ወጣቶችን በወንጌል ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ከዕለቱ…
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ላይ በዋለው ችሎት ታሪካዊ የሆነ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሁሉም 50 ስቴቶች ህጋዊ መሆኑን ደንግጓል፡፡ በቅድሚያ 3 ስቴቶች ብቻ ይፈቅዱት የነበረው የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ወደ 37 ስቴቶች አድጎ የቆየ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ግብረ ሰዶማዊነትን ጠቅልሎ ህጋዊ ተግባርና የሁሉም ዜጎች መብት እንደሆነ ወስኗል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጋብቻ ምን እንደሆነ ገለጻም ሆነ ትርጉም አልሰጠም፡፡ እንዲው በደፈናው ከተመሳሳ ጾታ ጋር ጋብቻ መፈጸም እንደሚቻልና የሁሉም አሜሪካዊ…
በ2006/2014 ዓ.ም. በተመረጡ መስፈርቶች ልህቀት ላሳዩ መዘምራን ዕውቅና እና ማበረታቻ ሊሰጥ ነው። ማበረታቻዎቹ ሚሰጡት ለተመረጡ ሶስት ዘማሪያን ሲሆን ፥ ሰጪውም አካል ማህሌት የመዝሙርና የሙዚቃ ፎረም አገልግሎት ይባላል። ስለፕሮግራሙ አላማና ስለ እውቅና ሰጪው አካል ለማወቅ ፥ የህብረቱን አስተባባሪዎች ፕሮፌሰር ጥላሁን አደራ ፥ ፓ/ር መላኩ ይገዙን እና ዘማሪ አዲሱ ወርቁን ዛሬ አንጋግረን ነበር። ፕሮፌሰር ጥላሁን ሲጀምሩ ፥ መዝሙር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ትልቅ ሥፍራ ጠቅሰው፥ በኢትዮጲያ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ ያሉ አብያተ…
በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አለም አቀፍ የወጣቶች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በኢትጲያ ተጀምሯል። ብሌዝ ሙቭመንት (Blaze movement) በመባል የተሰየመመው ይህ እንቅስቃሴ በምድራችን ላይ መንፈሳዊ ተሃድሶን ለማምጣት ታስቦ የተመሰረተ ነው። ይህም መንፈሳዊ ተሃድሶ በኛ ዘመን ይሆናል ብለን እናምናለን በማለት የእንቅስቃሴው መስራቾች ይናገራሉ፡፡ ብሌዝ ማለት የሚቀጣጠል እሳት ማለት ሲሆን በወንጌል የሚቃጠሉ ወጣቶችን ለማፍራት ትልቅ ራዕይን ሰንቋል። እንደሚታወቀው ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢተዮጲያ ሕዝብ ወጣት ነው ይሁን እንጂ አብዛኛው ወጣት በተለያየ ነገር ተጠምዶ ይገኛል፡፡ ብሌዝ አለም አቀፍ…
በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የሚመክር አውደ ጥናት እና የምክክር መድረክ ነገ ከሰኔ 5 እና 6 2007 ዓ.ም. በአቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ ይጀምራል። በኢትዮጵያ የሚገኙ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በእግዚአብሔር ጸጋና ርዳታ እግዚአብሔርን መንግሥት የማስፋፋት ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም አሁን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ሲመዘን በምድሪቱ ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር እንዳይቻል እና የእግዚአብሔር ስም እንዲሰደብ የሚያደርጉ አሳሳቢ ጉዳዮች መኖራቸው ግልጽነው፡፡ በዚህም ምክንያት ታሪካዊና አስፈላጊ የሆነ ዐውደ ጥናት እና…

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 33 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.