You are here: HomeSocial Issues ወላጅ አጥ ህጻናትን የምናገለግልበት 10 ተግባራዊ መንገዶች

ወላጅ አጥ ህጻናትን የምናገለግልበት 10 ተግባራዊ መንገዶች

Written by  Friday, 06 November 2015 19:13

በአማካኝ በአለማችን ላይ150 ሚሊዮን የሚሆኑ ወላጅ አጥ ህጻናት ይኖራሉ። እአአ በ 2014 የነበረው መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህ ልጆች እጅ ለእጅ ቢያያዙ የምኖርበት ምድር 4 ግዜ ክብ ይሰራሉ ተብሎ ይገመታል። በ ሐገራችንም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በአማካኝ 4.9, ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት ወላጆቻቸውን አጥተዋል። በአለማችን ላይ በየ2 ደቂቃ ሕጻናት ህይወታቸውን ያጣሉ። በየቀኑ በHIV ADIS አማካኝነት 6 ሺህ የሚሁኑ ሕጻናት ወላጅ አጥ ይሆናሉ፤ ይህ ማለት በየ14 ሰከንዱ አንድ ሕፃን ወላጅ አጥ ይሆናል ማለት ነው በአለማችን ላይ፤ 15.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት በAIDS አማካኝነት ነው ወላጅ አጥ የሆኑት። በየአመቱ የ5ኛ አመት ልደታቸውን ሳያዩ የሚሞቱት ሕጻናት በአማካኝ 5 ሚሊዮን ሲሆን፤ ይህ የሚከሰተው ደግሞ የተመጣጠን ምግብ ከማጣታቸው የተነሳ ነው።እኤአ በ 2010 በሕንድ ሐገር ብቻ 35 ሚሊዮን ወላጅ አጥ ሕጻናት ሲኖሩ፥ ይህ ማለት በሕንድ ሐገር ከሚኖሩ ከ 10 ሕጻናት አንዱ ወላጅ አጥ ነው። በአለማችን ላይ 854 ሚሊዮን ሰዎች በቂ ምግብ የላቸውም። ይህ ቁጥር ማለት በአሜሪካን ካናዳ እና በአውሮፓ የሚኖሩ ሰዎች የነዋሪዎች መጠን ነው።ከሰሀራ በታች ያሉ ሐገሮች ውስጥ በአመካኝ ከ 20 % በላይ የሚሆኑ አምራች ሐይሎች በ HIV ADIS ህይወታቸውን የተጠቁ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ወላጅ አልባ ልጆች የተነጠቁት ወላጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን፤ አስተማሪዎቻቸውን፤የጤና ባለሙያዎቻቸውን እንዲሁም መሪዎቻቸውን ነው። ዘወትር ከ7 ሕጻናት አንዱ ምግብ ሳይበላ ተርቦ ይተኛል።

 

እነዚህን ሁሉ መረጃዎችን በምንሰማበት ግዜ ልባችንን ሊታወክና ሊረበሽ ይችላል። ወይም ደግሞ ይህ ግልጽ ነው ምንም አያስደነግጠኝም ልንል እንችላለን።

 

ባለፉት ጥቂት አመታት ግልጽ የሆነልኝ ነገር፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ሲመለከት ይህን ትልቅ ቁጥር አይደለም የሚመልከትው። የሚመለከተው በራሱ አምሳል የሰራውን ሰውን ነው። እርሱ የእያንዳንዳቸውን፣ ስም ያውቃል የጸጉራቸውን ቁጥር፤ የልባቸውን ቁስል፣ ሳይቀር ያውቃል።

 

በአለም ውስጥ ከሚኖሩ 2.4 ቢሊየን ክርስቲያኖች 7% ብቻ አንድ ልጅ ልጃቻቸው ቢያደርጉ ይህ ትልቅ ቁጥር 0 ማድርግ ይቻላል። ምክንያቱም ሕጻናት ማደጊያ ውስጥ ሳይሆን ቤተሰብ ውስጥ ነው ማደግ ያለባቸው።

 

1. እንጸልይላቸው

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላለና፥ የሚፈልገውም ያገኛል መዝጊያንም የሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7:7-8

 

2. እንናገርላቸው

አፍህን ስለ ዲዳው ክፈት ተስፋ ስለሌላቸውም ሁለ ተፋረድ። አፍህን ክፈት ለድሀና ለምስኪን ፍረድ።ምሳሌ 31:8-9

 

3. ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን እናቅርብላቸው

ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?” ያዕቆብ 2:15-16

 

4. የሚንከባከቧቸውን እናግዛቸው

ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ ዕብራውያን 10:24

 

5. ከጉዳትና ከአደጋ እንታደጋቸው

እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፥ ድሀ አደጎችንና [አባት የሌላቸውን] ባልቴቶችን ይቀበላል። የሀጥያተኞችንም መንገድ ያጠፋል” - መዝ 146:9

 

6. በሚኖሩበት ቦታ እንጎብኛቸው

“ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች [አባት የሌላቸው] ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።” -ያዕቆብ 1: 27

 

7. በልግስና እንስጣቸው

“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም፡፡” - 2 ቆሮንቶስ 9:7

 

8. እናጽናናቸው

“...ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው...” 1ተሰልንቄ 5:14

 

9. የቤታችንንና የልባችንን በር ከፍተን ልጆቻችን እናድርጋቸው

“እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች [አባት ለሌላቸው] አባት ለባሌቴቶችም ዳኛ ነው። እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል” መዝ 68:5-6”

 

10. ቤተ ክርስቲያን እነርሱን እንድታገግል እናነሳሳ

“ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁለ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁለ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ፤ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴዎስ 28:18-20

 

ይህን ለምንድን ነው የምናደርገው? ችግርን ለመፋታት ሳይሆን የእያንዳንዳችን የወንጌል ጥሪ፤እንዲሁም የተልእኮአችን አንዱ አካል ስለሆነም ጭምር ነው ነው። ክርስትና ደግሞ ለሌሎች ሰዎች የማይታይ ከሆነ ከንቱ ነው። በአንፆኪያ ሲኖሩ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ የእምነት አባቶቻችን “ክርስቲያን” የተባሉት ለሰዎች በተገለጠው ስራቸው ነበር። የእግዚአብሔርም ቃል በግልጽ፤ ፍርድን እንድንፈልግ መናገር ለማይችሉት እንድንናገር ፤የሰዎችን ሸክም እንድንሸከም፤ አባት የሌላቸውን አባት እንድንሆናቸው፤ የበደልን እስራት አንድንፈታ፤ የቀንበርን ጠፍር እንድንለቅ፤ የተገፉትን አርነት እንድናወጣ ቀንበራቸውን ሁሉ እንድንሰብር ፤እንጀራችንን ለተራበ እንድንቆርስ፣ ስደተኞችን ድሆችን ወደቤታችን እንድናስገባ ፤የተራቆቱትን እናድናለብስ ፤ ይህን በምናደርግበት ግዜ ለምንኖርበት ምድር ፈውስ፣ እንዲሁም በጨለማ ለሚኖሩት ታላቅ ብርሀን፣ የእግዚአብሔር ታላቅ ክብር ማደሪያ እንሆናለን፣ ወደ እግዚአብሔር በምንጮህበት ግዜ “አቤት” በማለት ጽሎታችን በፍጥነት ይመለስልናል ፣የእግዚአብሔርን ምሪት በሕይወታችን በግልጽ እንረዳለን። መልካም የተባለ ነገር በሙሉ ያገኘናል፣የማያልቅ በረከት ቤታችን ውስጥ ይፈልቃል፣ በሕይወት ዘመናችንም ለረጅም ግዜ የፈረሱ ቅጥሮችን እናድሳለን ወደፊት የሚመጡ የብዙ ትውልድ መሰረት እናንጻለን።” ስማችንም ሰባራውን ጠጋኝ የመኖሪያ መንገድ አዳሽ እንባላለን።”

 

አንድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት በምንቆምበት ግዜ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄ ይጠይቀናል። የመጀመሪያው የሰጠውህንው ልጄን ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀብለሀል? ይህን ሁላችንም እናውቃለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሁለተኛው ደግሞ የሰጠውህን በረከት [መክሊት] ለሌሎች አካፍለሀል? እራሳችንን ለነዚህ መልሶች በየቀኑ ማዘጋጀት አለብን ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ጌታችን መቼ እንደሚመጣ ወይም እኛ ወደ እርሱ የምንሔድበትን ቀን ማናችንም ስለማናውቅ።    የእኔም ጸሎት ጌታችን ተመልሶ በሚመጣበት ግዜ አላውቅህም ሳይሆን “አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” ከሚለን ሰዎች እንድንሆን ነው። እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ይርዳን።

እርሶም በቤተክርስትያኖት የወላጅ  አጥ Orphan Sunday Coordinator ለመሆን የሚፈልጉ  ከሆነ እባክዎን በሚቀጥለው አድራሻ ያግኙን፣ በሚያደርጉት አገልግሎት አብረኖት ልንቆም እንፈልጋለን።

www.orphansunday.org

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

P.O.Box 15233

251 911 941261

Addis Ababa

                                                                          Ethiopia

Seen 9171 times Last modified on Saturday, 07 November 2015 08:38
Belay T.Gebru

I am nobody trying to tell everybody about Somebody.

Website: hftf.org Email This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Nahu's Corner

 

 

 

.

Right Now

We have 94854 guests and no members online

About Us

Semayawi Thought is an online magazine published in Amharic and English, focused on contents to spiritual and personal growth.